The Amhara Association of Nebraska (AAN) is a 501(C) (3) nonprofit organization registered in the state of Nebraska. Amhara Association of Nebraska is primary opposed to Abiy Ahmed government of Ethiopia which is engaged in Amhara genocide, displacement and ethnic cleansing. Consequently, AAN is unifying with other similar Amhara associations to expose Abiy Ahmed’s atrocity to the world at large through diplomacy and advocacy.

In addition, to enhance awareness of Amhara genocide, AAN has developed a website, with multiple pages such as Fano page, recent developments, members’ commentary, announcements, research articles, and video gallery.
Contact
We maintain contact through AAN email at [email protected]. We respond back
within 24-hour period.

Mission Statement
The mission of the Amhara Association of Nebraska is to demand unconditional and immediate stoppage of Amhara genocide, displacement, and ethnic cleansing in Ethiopia. The Amhara Association of Nebraska works with other global Amhara associations to urge world governments to isolate the Abiy government from participating in international bilateral relations, impose economic sanctions, travel restrictions, and an arms embargo, and possibly depose him from power, apprehend him, and send him to the international criminal court.
Goals

1.Inform and educate the Ethiopian people and the global community about Amhara genocide, displacement, and ethnic cleansing.

2. Plan, organize, and implement means and ways to stop Amhara genocide, displacement, and ethnic cleansing.

3. Fundraise to help the displaced, the orphaned, the handicapped, and the elderly have shelter, food on the table, and possibly resettlement.

Fano Page

The Fano page displays video and audio messages from the Fano leaders, current interviews held with the Fano leadership, and commentaries made from Fano supporters.

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ)

የፖለቲካ ፕሮግራም ሰነድ
(ማኒፌስቶ)

አፋሕድ

የአማራን ሕዝብ የህልውና አደጋ ይቀለብሳል፣

ፍትሕ ያሰፍናል፣
ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ይገነባል!

ጥር ፳፻፲፯ ዓ.ም.
ከትግሉ ሜዳ!

i

መቅድም

ከግማሽ ክፍለ-ዘመን በላይ በአማራ ሕዝብ ላይ በትርክት፣ በህግ እና በአስተዳደራዊ መዋቅር የተደገፈ መንግሥት መር የዘር
ማጥፋት ወንጀል እየተፈፀመበት ነው። ደረጃውና ሁኔታው ይለያይ እንጅ በኢትዮጵያ ሰማይ ስር በሁሉም ብሄረሰቦች ላይ
በማንነታቸው ምክንያት በጅምላ የሚገደሉ፣ ተወልደው ባደጉበት ቀዬ በግፈኞች የሚፈናቀሉና ሀብትና ንብረታቸው
የሚወድምባቸው በርካቶች መሆናቸው ይታወቃል።
ይህ ሥር የሰደደ ጭቆናና አፈና እንዲሁም የዘር ማጥፋት ወንጀል አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍል
ተቃውሞ ገጥሞታል። በተለይ ተጨባጭ የህልውና አደጋ የተጋረጠበት የአማራ ሕዝብ ህልውናውን ለማስጠበቅ በተከታታይ
በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞውን ቢገልጽም መፍትሄ ባለማግኘቱ፣ ይባሱን አገዛዙ በእብሪት ጦርነት በማዋጁ ወደ ሁሉን
አቀፍ ትግል እንዲገባ ተገዷል።
የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል የመነጨው እኩልነትን፣ ፍትሕንና ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ስለሆነ ከየትኛውም ማኅበረሰብ
ጋር ምንም ዓይነት ቅራኔ የለበትም። የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅትም እነዚህን የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች መሰረት አድርጎ
ትግል የሚያካሂድ በመሆኑ ከማንኛውም ማህበረሰብና የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር በጋራ ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን
ይገልፃል።
በመሆኑም በአሁኑ ወቅት ጨፍጫፊና አገር አፍራሽ የሆነውን አገዛዝ ከሚታገሉና ከህዝባችን ጥቅምና ፍላጎት ጋር የማይጋጭ
የፖለቲካ ፕሮግራም ካላቸው አካላት ጋር አብረን ለመሥራት ዝግጁ መሆናችንን እየገለፅን ይህ ሰነድም እንደአስፈላጊነቱ
ከሕዝብ በሚመጡ አስተያየቶች ማሻሻያ ወይም ማስተካከያ የሚደረግበት ሆኖ ይቀጥላል።

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) የፖለቲካ ፕሮግራም ሰነድ | AFPO’s Manifesto

ii

ማውጫ

ርዕስ

ገጽ
ምዕራፍ አንድ: የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት የትጥቅ ትግል መነሻ ምክንያቶች እና መዳረሻ ግቦች……………………………………3
1.1 አንኳር የትግል መነሻዎች………………………………………………………………………………………………………………3
1.1.1 በአማራ ሕዝብ ላይ ዘር ማጥፋት መፈፀሙና ለህልውና አደጋ መጋለጡ ኢሕአዴግ (Genocide& Unequivocal existential threat) ………………………………………………………………………………………………………………………………………………………3
1.1.2 የፖለቲካ ክህደት(Political Denial)……………………………………………………………………………………………4
1.1.3 ለአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች ተገቢዉን መልስ አለመስጠት…………………………………………………………………………..5
1.2 የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት የትግል ግቦች/የሚታገልላቸው ጥያቄዎች……………………………………………………………5
ምዕራፍ ሁለት: የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ቁልፍ መርሆዎች……………………………………………………………………… 10
2.1 የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነትን ማስጠበቅ…………………………………………………………………………………………… 10
2.2 እኩልነትና ነፃነት……………………………………………………………………………………………………………………… 10
2.3 የሃይማኖትና የመንግሥት መለያየት …………………………………………………………………………………………………. 10
2.4 በትብብር መሥራት……………………………………………………………………………………………………………………. 10
ምዕራፍ ሶስት: የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ፕሮግራሞች……………………………………………………………………………… 11
3.1 የፖለቲካ ፕሮግራም……………………………………………………………………………………………………………………..11
3.1.1 ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታና የሰብዓዊ መብቶች መከበር………………………………………………………………………11
3.1.2 የመንግሥት ስልጣን አወቃቀር ………………………………………………………………………………………………………11
3.2 የኢኮኖሚ ፕሮግራሞች…………………………………………………………………………………………………………………. 13
3.2.1 የመሬት ባለቤትነት……………………………………………………………………………………………………………………. 13
3.2.2 ግብርና……………………………………………………………………………………………………………………………………14
3.2.3 ኢንዱስትሪ………………………………………………………………………………………………………………………………..14
3.2.4 ንግድ……………………………………………………………………………………………………………………………………… 15
3.2.5 መሰረተ ልማቶች ………………………………………………………………………………………………………………………….. 15
3.2.6 የውኃ ሐብት……………………………………………………………………………………………………………………………… 15
3.2.7 የቱሪዝም ሃብት…………………………………………………………………………………………………………………………… 15
3.3 ማህበራዊ ፕሮግራሞች…………………………………………………………………………………………………………………………………………16
3.3.1 ትምህርት……………………………………………………………………………………………………………………………………16
3.3.2 ጤና …………………………………………………………………………………………………………………………………………16
3.3.3 ባህል…………………………………………………………………………………………………………………………………………17
3.3.4 ሚዲያ ………………………………………………………………………………………………………………………………………………..17

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) የፖለቲካ ፕሮግራም ሰነድ | AFPO’s Manifesto

1

መግቢያ
የአማራ ሕዝብ ከዳማት ጀምሮ እስከ 20ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን የዘለቀ የሀገረ መንግሥት ግንባታና ጥልቅ ታሪክ ያለው
ሕዝብ ነው። ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ህዝቦች ጋር ሆኖ የአማራ ሕዝብ ከሺህ ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ታሪክ ብቻ ሳይሆን
ገናና የግዛት አንድነትና ልዕለ ኃያልነትን መፍጠር የቻለ፤ በአለም ላይ ጉልህ ከሚባሉ የግሪክ፣ የሮም፣ ፋርስና የቻይና
ስልጣኔዎች የሚስተካከል ታሪክ ያለው ነው።

የአክሱም ዘመን መንግሥት ሀውልቶች፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ-ክርስትያናት፣ የጣና ጥንታዊ ገዳማት፣ የጎንደር ቤተ-
መንግሥት ወዘተ የአማራ ሕዝብ ቀደምት ስልጣኔ ባለቤት መሆኑ ቋሚ ምስክሮች ናቸው። በተለይም በመካከለኛው ዘመን

በአፄ አምደ-ጽዮንና አፄ ዘርዓያቆብ ዘመነ መንግሥት የአማራው ፍፁም የከፍታ ዘመን የነበረ ሲሆን በስነ-ፅሁፍ፣ በስነ-ፈለግ፣
በወታደራዊ ሳይንስ፣ በአስተዳደር ጥበብና በሌሎችም ዘርፎች ከፍተኛ እምርታ የታየበት ወቅት ነበር።
የአማራ ሕዝብ በስነ-ህንፃ፣ በዘመን አቆጣጠር፣ በስነ-መንግሥት ፣ በስነ-ጥበብ ለተከታታይ ሺህ ዘመናት የዳበረ ሥልጣኔ
ባለቤት ቢሆንም ሂደቱ ግን አልጋ በአልጋ አልነበረም። ይልቁንስ ከውጭ እና ከውስጥ ከሚነሱ ጠላቶች በቀጥታና
በተዘዋዋሪ ከፍተኛ ጥቃት እየደረሰበት ነበር። ኦቶማን ቱርክ፣ ግብፅ፣ ሱዳን፣ እንግሊዝ፣ ጣሊያንና በእነዚህ ሀገራት
በሚታገዙት የሀገር ውስጥ የጎሳ አክራሪና የኃይማኖት ጽንፈኞች ምክንያት መጠነ-ሰፊ ውድመት ደርሶበታል። ይሁን እንጅ
የአማራ ሕዝብ ራሱን በብቃት በመከላከል ህልውናውን በዘላቂነት ማስጠበቅ ችሏል።
ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከውስጥ እና ከውጭ በተነሱ አማራ ጠል ቡድኖች አማካኝነት የአማራ ሕዝብ እንደ ቅኝ ገዥ፣
እንደ ጨቋኝ፣ እንዲሁም የነጮች ጠላት እንደሆነ ተድርጎ የጥላቻ ዘመቻ ተከፍቶ፣ “ኢትዮጵያ የብሔሮች እሥር ቤት ናት”
የሚል ትርክት ተሰርቶ ለመጠነ ሰፊ ጥቃት እንዲጋለጥ ተደርጓል። የአማራ ሕዝብ የአባቶቹን አጽመ-ርስት ጠብቆ ባቆየ እንደ
ወራሪና ቅኝ ገዥ በመቁጠር የማያባራ ፕሮፖጋንዳ ተሰርቶበታል። የህዝባችንን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ
እንዲሁም ታሪካዊ መስተጋብርን ግምት ውስጥ ሳያስገባ ከውጭ ተጭኖ የገባው የግራ ዘመም እሳቤ በአማራ ሕዝብ ላይ
ያነጣጠረ ጥላቻ እንዲወለድና ይህም አሁን ላይ በተጨባጭ እየደረሰ ወዳለው እልቂት እንዲያመራ ያለመታከት
ተሰርቶበታል።
የማርክሲዝም ሌኒንዝምን ርዕዮተ-ዓለም ተከትሎ በኢትዮጵያ ያቆጠቆጠው ጎሳ ተኮር የፖለቲካ አስተሳሰብ ለረጅም ጊዜ
በአማራ ሕዝብ ላይ ይህ ቀረሽ የማይባል እልቂትና የማህበራዊ፣ የፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስን አምጥቷል። የአማራ
ሕዝብ ይህን በትርክት፣ በህግ እና በሥርዓት ታግዞ የሚፈጸመውን መጠነ ሰፊ ጥቃት ለአመታት ሲታገል ቆይቷል።
በመጨረሻም ከመላዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በጋራ ባደረገዉ የተቀናጀ ትግል በሕወኃት የበላይነት የሚመራውን ጨቋኙን
እና አፋኙን የኢሕአዴግን ስርዓት ከዙፋኑ ለመገረሰስ ተችሏል።
ይሁን እንጅ በአመዛኙ በአማራ እና በኦሮሞ ሕዝብ (ኦሮ-ማራ) ጥምረትና ትብብር የመጣው ይህ የስርዓት ለዉጥ አሳዛኝ
ክህደት ተፈጽሞበታል። የሕዝብን ትግል በሆዳቸው መሸጥ የለመዱት የብአዴን ሰዎች የአማራን ሕዝብ ትግል በመሸጥ
የኢትዮጵያ በተለይም የአማራ ሕዝብ ጠላት የሆነውን ኦህዴድ መራሽ የብልፅግና ስርዓትን አዋልደዋል።

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) የፖለቲካ ፕሮግራም ሰነድ | AFPO’s Manifesto

2
ፋሽስታዊ እሳቤ ያለው የአብይ አህመድ አገዛዝ ወደ ሥልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ ማንነትን መሠረት ያደረገ ዘር ማጥፋት፣
ማፈናቀል፣ ንብረት ማውደም፣ ተቋማትን ማፍረስ፣ ታሪክና ቅርስ ማጥፋት፣ የሀገርን ሉዓላዊነት ማስደፈር እና ሌሎችንም
በደሎች በኢትዮጵያዊያን በተለይም በአማራ ሕዝብ ላይ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ከሁሉ በላይ ደግሞ ከሃምሌ 28፣ 2015 ዓ.ም
ጀምሮ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ በአማራ ሕዝብ ላይ ይፋዊ ጦርነት በመክፈት በህዝባችን ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል
እየፈጸመ፣ ኢትዮጵያንም እያፈራረሰ ይገኛል።
ይህን በህዝባችን ህልውና እና በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የታወጀን የዘር ማጥፋት እና ሀገር የመበተን ጦርነት ለመመከት
የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል እያደረገ ይገኛል። ይሁን እንጅ የህልውና ትግሉ ጉዞ ሲመረመር ግልጽ የሆነ የትግል
መስመርና ግብ የተቀመጠለት አልነበረም። ይህን ግምት ውስጥ በማስገባት የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) ይህን
የትግል ፍኖተ- መርህ (ማኒፌስቶ) አዘጋጅቷል፡፡

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) የፖለቲካ ፕሮግራም ሰነድ | AFPO’s Manifesto

3

ምዕራፍ አንድ

የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት የትጥቅ ትግል መነሻ ምክንያቶች እና መዳረሻ ግቦች

1.1 አንኳር የትግል መነሻዎች
የአማራ ሕዝብ ለኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት ግንባታና ለሀገር ህልውና መጠበቅ የተጫወተው የአንጋፋነት ሚና እንደ ወንጀል
ተቆጥሮበት በቄሳራዊያን ሃይሎች (ቅኝ ገዥዎች) ጥርስ ተነክሶበት ታሪኩ፣ ባህሉና ዕሴቱ እንዲጠለሽ፤ እንዲሁም በሌሎች
የኢትዮጵያ ህዝቦች እንዲጠላ አደገኛ ፀረ አማራ ትርክት ተፈጥሮ በስፋት ተሠርቶበታል።
በዚህም የተነሳ የአማራ ሕዝብ በትርክት፣ በህግ እና በሥርዓት የታገዘ መጠነ ሰፊ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞበታል፣
እየተፈጸመበትም ይገኛል። በተለይ ሕወኃት መራሹ ኢሕአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣበት ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ በአማራ ሕዝብ
ላይ የሚደርሰው የዘር ማጥፋት ወንጀል በመላው የአማራ ሕዝብ ሥር እየሰደደ እና አድማሱን እያሰፋ መጥቷል። በ2010
ዓ.ም ሕወኃት ሰራሹ ኢሕአዴግ ከስልጣን ሲወርድ በቦታው የተተካው ኦህዴድ መራሹ አገዛዝም በአማራ ሕዝብ ጥላቻ
ተኮትኩቶ ያደገ በመሆኑ የአማራ ሕዝብን ለከፋ የህልውና አደጋ እንዲጋለጥ አድርጓል።
አፋሕድ እንደ አታጋይ ድርጅት በህዝባችን ላይ የተደቀነውን የሕልውና አደጋ ቀልብሶ የህዝባችንን ነፃነት ለማረጋገጥ
የትግሉን መነሻ ምክንያቶች እና መድረሻ ግቦችን በግልጽ ማስቀመጥ በጣም አስፈላጊ ነው ብሎ ያምናል። ከዚህ አንፃር
የአማራ ሕዝብ ወደ ትጥቅ ትግል እንዲገባ ያደረጉት ዋና ዋና ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው።
1.1.1 በአማራ ሕዝብ ላይ ዘር ማጥፋት መፈፀሙና ለህልውና አደጋ መጋለጡ ኢሕአዴግ (Genocide&
Unequivocal existential threat)

የአማራ ሕዝብ ከትናንቱ የኢሕአዴግ አገዛዝ የቀጠለ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈፀመበት ይገኛል። በዘመነ ኢሕአዴግ
የአማራው ሕዝብ በበደኖ፣ በአርባ ጉጉ፣ በወተር፣ በጅማ፣ በወለጋ፣ በመተከል፣ በወልቃይት፣ በጠለምት፣ በራያ፣ በደራ
እንዲሁም በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች ከፍተኛ እልቂትን አስተናግዷል። በሕወኃት መራሹ ኢሕአዴግ አገዛዝ የሚፈፀመውን
የህዝባችንን እልቂት ለመታደግ ህዝባችን ብርቱ ዋጋ ከፍሎ አገዛዙን ቢያስወግድም ከኢሕአዴግ አብራክ በወጡ፣ ሴረኛና
ፅንፈኛ የጎሳ ብሄርተኞች ለውጡን በመጥለፍ ራሳቸውን ብልጽግና ብለው በማደራጀት ለኢትዮጵያዊያን በተለይም ለአማራ
ሕዝብ የባሰ የጭቆና ሥርዓት እንዲወለድና የከፋ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲፈፀም አድርገዋል።
የአማራ ሕዝብ በግንባር ቀደምትነት ብርቱ ዋጋ ከፍሎ ያመጣው ለውጥ ክህደት ተፈፅሞበት በአጭር ጊዜ ወደ ነውጥ
ተቀይሮ መንግሥት መር የጅምላ ግድያ አድማሱን አስፍቶ በሻሸመኔ፣ በጅማ፣ በወለጋ፣ በአርሲ፣ በአጣዬ፣ በመተከል፣
በአዲስ አበባና በሌሎችም አካባቢዎች ከፍተኛ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል፣ አሁንም እየተፈፀመ ይገኛል። በተለይም
ይህ የዘር ማጥፋት፣ የዘር ማጽዳትና የዘር ማመናመን ወንጀል የሚፈፀመው በዋናነት የአገዛዙ ቁንጮ አመራሮች በወጡበት
የ”ኦሮሚያ” ክልል መሆኑና ህዝባችን ለሚያነሳው የህልውና ጥያቈ የፌዝና ቀልድ ምላሽ መስጠቱ ኦህዴድ መራሹ የብልጽግና

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) የፖለቲካ ፕሮግራም ሰነድ | AFPO’s Manifesto

4
አገዛዝ ለአማራ ሕዝብ መገደልና መሳደድ እንዲሁም ለኢትዮጵያ መፈራረስ ህጋዊና መዋቅራዊ ድጋፍ እያደረገ ለመሆኑ
ማረጋገጫ ነው።
በአሁኑ ጊዜ ከኦሮሚያ ክልል ብቻ ከሞት እያመለጡ፣ ኃብትና ንብረታቸውን ትተው የሚሰደዱት አማራዎች ብዛት
በሚሊዮኖች የሚቆጠር ሆኗል። በአለም ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን የሚከታተለውና የሚመረምረው
ድርጅት(Genocide watch) ለዘር ማጥፋት ወንጀል ተጋልጠዋል ብሎ ካስቀመጣቸው 20 ሀገራት ውስጥ አንዷ ኢትዮጵያ
እንድትሆን አድርጓታል። በዚህ ዓለም አቀፋዊ ድርጅት መስፈርት መሰረት አንድ ሀገር ለዘር ማጥፋት ወንጀል ተጋልጧል
ብሎ ለመደምደም ስምንት ደረጃዎች መሟላት አለባቸው። በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለው የዘር ማጥፋት ወንጀልም
እነዚህን ስምንት መስፈርቶች በትክክል የሚያሟላ መሆኑን አረጋግጠናል። የአማራን ሕዝብ ለማጥፋት ሆን ተብሎ ትርክት
ተሰርቶበት፣ ዋና አቀንቃኝና አጫፋሪ ተፈጥሮለት አማራን በአካል፣ በስነ-ልቦና፣ በኢኮኖሚ፣ በእሴት፣ በባህል፣ በቋንቋና
በኃይማኖት ጭምር የማዳከም ሥራ ተሰርቶበታል፣ አሁንም እየተሰራበት ይገኛል። ራሱን እንዳያደራጅ ለመበተንና
በመጨረሻም ለማጥፋት እየተሰራ መሆኑም የአደባባይ ሚስጥር ነው። የዘር ማጥፋት ወንጀሉ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ
እስካሁን ድረስ በተጠናና በተቀናጀ መልኩ ተቋማዊ ጥቃት እየተፈፀመበት መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል።
ጎሳ ተኮሩና አማራ ጠል የሆነው የኦህዴድ-ብልጽግና አገዛዝ አማራን በተለዬ ሁኔታ ለጥቃት ከማጋለጡም በላይ ከምድረ-ገፅ
ለማጥፋት ጦርነት አውጆበታል። ይህ አገዛዝ የአማራ ሕዝብ መከታ የሆነውን ልዩ ኃይል በተለየ ሁኔታ እንዲፈርስና ትጥቁን
እንዲፈታ ካደረገ በኋላም የፋኖንና የአርሶ አደሩን መሳሪያም ለመሰብሰብ ወደ ተግባር የገባው ያለማንም ከልካይ አማራ
የሚባልን ሕዝብ ከምድረ-ገጽ ለማጥፋት መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነበር።
በኦሮሚያና በአንዳንድ ክልሎች ተወስኖ የነበረው የአማራ ጭፍጨፋ አድማሱን አስፍቶ በሁሉም የመንግሥት የፀጥታ
ኃይሎች “አማራ ክልል” ላይ ጅምላ ጭፍጨፋ እየተደረገበት ይገኛል። ወርቅ ላበደረ ጠጠር እንዲሉ የአማራ ወጣት ብርቱ
ዋጋ ከፍሎ ወደ ስልጣን ያመጣቸው አመራሮች አማራን ከምድረ-ገፅ ለማጥፋት “አማራ ክልል” ላይ በሁሉም ዞኖችና
ወረዳዎች ያለምንም ልዩነት ኔትወርክ በመዝጋት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ እና የአማራ ሕዝብን በኮማንድ ፖስት
አስተዳደር በመጠርነፍ ይፋዊ ጦርነት ከፍተው በድሮንና ሜካናይዝድ ጦር በተደገፈ ዘመቻ የአማራ ሕዝብን ለህልውና
አደጋ እንዲጋለጥ አድርጓል።
1.1.2 የፖለቲካ ክህደት (Political Denial)
በርካታ የአማራ ወጣቶች በግንባር ቀደምትነት ብርቱ ዋጋ ከፍለው በ2010 ዓ.ም ፖለቲካዊ ለውጥ እንዲመጣ ቢያደርጉም
የአማራ ሕዝብ በተከፈለው ዋጋ ልክ ተገቢውንና ፍትሃዊ የሆነ የፖለቲካ ውክልና (ስልጣን) አላገኘም። በተቃራኒው ሀቀኛ
የአማራ አመራሮችን በሴራ ከማስገደል ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ ፖለቲካዊ ሸፍጥ ተፈጽሞበታል። የአማራ ሕዝብም በየቦታው
እንዲገደልና እንዲፈናቀል ተደርጓል። የፌደራል መንግስቱንም ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የኦህዴድ ቡድንና ምስለኔዎቹ
ተቆጣጥረው የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽመዋል፣ አሁንም በመፈፀም ላይ ይገኛሉ።
በሀገረ መንግስቱ ግንባታ ላይ ከፍተኛ ሚና የነበረው የአማራ ሕዝብ ለዘመናት በሰላማዊ መንገድ ሲያነሳቸው ለነበሩ ፍትሃዊ
ጥያቄዎች መልስ ከመስጠት ይልቅ መንግሥት መር የሆነ ከፍተኛ የህልውና አደጋ እንዲጋረጥበት ተደርጓል። በተጨማሪም
የወሰንና የማንነት ጥያቄዎችን ከህዝቡ ፍላጎት ፍጹም ተቃራኒ በሆነ መልኩ ለፖለቲካ ቁማር መጫዎቻ በማድረግ እንዲሁም
ከክልሉ ውጭ የሚኖሩ አማራዎች በተለያየ ሁኔታ ለከፍተኛ እልቂትና ቀውስ እንዲጋለጡ ተደርጓል።

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) የፖለቲካ ፕሮግራም ሰነድ | AFPO’s Manifesto

5

1.1.3 ለአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች ተገቢዉን መልስ አለመስጠት
የአማራ ሕዝብ ለረጅም ጊዜ ሲያነሳቸው የነበሩ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጥያቄዎችን መመልስ የሚችል
ስርዓት አለመኖሩ ብቻ ሳይሆን ህዝቡን ለተጨማሪ ችግር የሚዳርግ አገዛዝ ተፈጥሮ ህዝባችን ለከፋ የህልወና አደጋ
እንዲጋለጥ ተደርጓል። የአማራ ሕዝብ የሚያነሳቸው በርካታ ጥያቄዎች ቢኖሩም መሰረታዊ ጥያቄዎቹ ግን የሚከተሉት
ናቸዉ፡፡ በአማራ ላይ የተጋረጠውን የህልውና አደጋ መቀልበስ፣ ዘላቂ ሰላምና ፍትሕን ማስፈን፣ ፀረ-አማራና ሀገር አፍራሽ
የሆነውን ህገ-መንግሥት መቀየር፣ ትክክለኛ የሆነ የሕዝብ ቆጠራ ማካሄድና የበጀት ቀመርን ማሻሻል፣ የሀሰት ትርክትን
ማረምና ገዥ ብሄራዊ ትርክት ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ፣ የወሰንና የማንነት ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ማድረግ፣
እኩል የዜግነት መብትን እና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ፣ እንዲሁም ህዝቦች በጸጋቸው ልክ መልማት እንዲችሉ መሥራት
ሲሆን ዝርዝሩም ከዚህ በታች ቀርቧል።
1.2 የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት የትግል ግቦች/የሚታገልላቸው ጥያቄዎች
1ኛ. በአማራ ሕዝብ ላይ የተጋረጠውን የህልውና አደጋ መቀልበስ
የአማራ ሕዝብ ከትናንቱ የቀጠለ ጭፍጨፋና የዘር ፍጅት እየተካሄደበት ይገኛል። ይህ የተቀነባበረ መንግሥት መር
ጭፍጨፋ በሰላማዊ መንገድ ለመመለስ የተደረጉት ጥረቶች በሙሉ ውጤታማ አልሆኑም። በዚህም የተነሳ የአማራ
ሕዝብ ተፈጥሯዊ የመኖር መብቱን ለመከላከልና ራሱን ከእልቂት ለመታደግ የትጥቅ ትግል ጀምሯል። ከዚህ አንፃር
የአማራን ሕዝብ ህልውና ለማስጠበቅ የሚደረገውን የትጥቅ ትግል ከፊት ሆኖ እየመራ በአማራ ሕዝብ ላይ በሰማይና
በምድር እየዘነበበት ያለውን ጦርነት እንደአመጣጡ ለመመከት አፋሕድ አልሞ እየሰራ ይገኛል። ከሕዝብ እምቢተኝነት
እስከ ተደራጀ የትጥቅ ትግል ያሉትን ሁሉንም አማራጮች በመጠቀም አፋሕድ በአማራ ሕዝብ ላይ የተጋረጠውን
የህልውና አደጋ ለመቀልበስ የጀመረውን ትግል አጠናክሮ ይቀጥላል፣ ወደፊትም ከሚመጣበት የህልውና አደጋ ራሱን
ለመጠበቅ አፋሕድ የህልውና ዘብ ሆኖ የሚቆም ይሆናል።
2ኛ. ዘላቂ ሰላምና ፍትሕን ማስፈን
የአማራ ሕዝብ ከሰማይ በታች ያሉ አረመኔያዊ ድርጊቶች ሁሉ ተፈፅመውበታል። አማራነታቸው እንደ ጥፋት ተቆጥሮ
በሀገሪቱ በሚገኙ በግልጽ በሚታወቁ እና በማይታወቁ እስር ቤቶች በመንገላታት ላይ የሚገኙ ንጹሃን አማራዎች
በአስቸኳይ እንዲፈቱ፤ እንዲሁም እነሱ እና ካሁን በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ ካለጥፋታቸው ታስረው የተንገላቱ አማራዎች
ፍትሕ እንዲያገኙ ማስቻል አንዱ የትግላችን ግብ ነው።
በብልጽግና እና በግብረ-አበሮቹ ሴራ አማካኝነት ከደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ደብዛቸው የጠፉ ሴት ተማሪዎችን ጨምሮ
በተለያዩ ጊዜያት የተሰወሩ አማሮች ዕጣ ፈንታቸው ተጣርቶ፤ በሕይወት ካሉ ከቤተሰቦቻቸው እንዲገናኙ፤ በሕይወት
ከሌሉም ቤተሰቦቻቸው በአግባቡ እንዲረዱ እና ፍትሃዊ ካሳ እንዲያገኙ፣ ወንጀለኞችም ለፍርድ እንዲቀርቡ ይደረጋል::
በተደጋጋሚ በአማራ ሕዝብ ላይ ለተደረጉት ሕገ-ወጥ ወታደራዊ ዘመቻዎች እና በዘመቻዎቹ ለጠፋዉ የሰው ሕይወት፣
ንብረት፣ እንዲሁም በዚያ ምክንያት ለተጎዳዉ ኢኮኖሚ፣ ለተስተጓጎሉ የትምህርት አና የጤና አገልግሎቶች፣ በነዚህም
ምክንያት ለመከኑ ዕድሎች ሕዝቡና ተጎጂ ቤተሰቦችም ተገቢ ካሳ እንዲከፈላቸዉ ማድረግ የትግላችን አንዱ ግብ ነው።

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) የፖለቲካ ፕሮግራም ሰነድ | AFPO’s Manifesto

6
እንደ ሀገር ሰላማዊ የህዝቦች መስተጋብር ይኑር ከተባለ የሽግግር ፍትሕ ተግባራዊ መደረግ አለበት ብለን እናምናለን። ይህ
የሽግግር ፍትሕ ሦስት (3) የአፈፃፀም አቅጣጫዎችን መያዝ ይኖርበታል።

  1. እውነትን ማውጣት (uncover the truth): የመጀመሪያው በአማራ ሕዝብ ላይ ለደረሰበት ግፍና በደል በቂ
    ጥናት አድርጎ እውነቱን በማውጣት ብሄራዊ እውቅና መስጠት ነው። አሰከፊ የተባሉት የዘር ጭፍጨፋዎች
    በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች መደረጉን በብሄራዊ ደረጃ በአዋጅ በማመን ይቅርታ መጠየቅና ለመጪው ትውልድ
    አስተማሪ ሆኖ እንዲያልፍ ብሔራዊ የሰማታት ቀን ማወጅ ያስፈልጋል።
  2. ወንጀለኞችን ወደ ህግ ማቅረብ (Justice): ሁለተኛው ምዕራፍ ጥቃቱን ያደረሱ፣ ያቀነባበሩና የመሩ ግለሰቦች
    እንዲሁም ቡድኖች በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ ነው።
  3. ብሔራዊ እርቅ እና ካሳ (National Reconcilation and Reparation): በሶስተኛ ደረጃ ጉዳት ለደረሰባቸው
    ወገኖች ስነ-ልቦናዊና ኢኮኖሚያዊ ካሳ መስጠት እና ብሔራዊ እርቅ ማካሄድ ሲሆን ይህም ማለት ተፈናቃዮችን
    ወደ ነባር መኖሪያ ቦታቸው በመመለስ ማቋቋምን ጭምር ያካትታል።
    በተጨማሪም በዘላቂነት የህዝባችን ሰላምና ፍትህ እንዲረጋገጥ ለሁሉም እኩል የሚቆም የፀጥታ መዋቅር በመዘርጋት
    የጥይት ድምጽ የማይሰማበትን ሰላማዊ ሀገርን መገንባት ያስፈልጋል።
    3ኛ. ፀረ-አማራና ሀገር አፍራሽ የሆነውን ህገ-መንግሥት መቀየር/ማሻሻል
    ህገ መንግሥት የአንዲት ሀገር የምትተዳደርባቸው ህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ነው። ይህ ማለት ህገ መንግስቱን የሚቃረን
    ማንኛውም ህግ፣ ደንብ እና መመሪያ ተግባራዊ መሆን አይችልም ማለት ነው። ይሁን እንጅ የአማራ ሕዝብ ተነግሮ
    የማያልቅ ስርዓታዊ በደልና መድሎ የደረሰበት በኢሕአዴግ ሰራሹ ህገ መንግሥት የተነሳ ነው። የበርካታ ሀገራት ተሞክሮ
    እንደሚያሳየው ህገ-መንግሥት የማውጣት ሂደት አራት ዋና ዋና ደረጃዎችን ማለትም የማርቀቅ (Drafting)፣ የውይይት
    (Deliberation)፣ የአቀባበል/ማላመድ (Adoption) እና ማፅደቅ (Ratification) የሚያካትት ነው። ይሁን እንጅ
    ኢሕአዴግ መራሹ መንግሥት ህገ መንግስቱን ሲያወጣ እነዚህን ሂደቶች ካለመከተሉም በላይ የአማራ ሕዝብ
    በየትኛውም ደረጃ በእውነተኛ ወኪሎች አማካኝነት አልተሳተፈም። ይባስ ብሎም አማራን ለመወከል በፕሮፌሰር አስራት
    ወልደየስ የተደራጀውን መላ አማራ ሕዝባዊ ድርጅትን (መአሕድ) አመራሮችን በማጥፋት በምትኩ ፀረ-አማራና የህወሓት
    ጉዳይ አስፈጻሚ የሆነውን ብአዴን የአማራ ሕዝብ ተወካይ እንዲሆን ተደርጓል። በመጨረሻም የአማራን ሕዝብ የካደ፣
    ኢትዮጵያንም አደጋ ውስጥ የከተተ ህገ-መንግሥት ሥራ ላይ ውሎ ሚሊዮኖችን ለሞትና ለስደት እንዲጋለጡ አድርጓል።
    ዝርዝር ጉዳዮቹ ወደፊት በህገ-መንግሥት ባለሙያዎች የሚብራራ ሆኖ በዚህ ሰነድ አምስት ዋና ዋና የህገ መንግስቱ
    ችግሮችና ለመቀየር ምክንያት የሆኑትን ለማሳየት ተሞክሯል።
    1ኛ. ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው የህገ-መንግሥት አወጣጥ ሂደቶችና ደረጃዎች ያላሟላ በተለይም የአማራን
    ሕዝብ የገፋና ያገለለ፣ በረቂቅ ዝግጅቱ ላይ ያልተወከለበትና ያልተሳተፈበት እንዲሁም በማፅደቅ ሂደቱም ላይ
    ያልነበረና ያላፀደቀው ስለሆነ፣
    2ኛ. አማራ ጠልና ተገንጣይ ኃይሎች ህገ-መንግሥት አፀደቅን ካሉም በኋላ “መጭው የጋራ እድላችን መመስረት
    ያለበት ከታሪካችን የወረስነውን የተዛባ ግንኙነት በማረም. . .” በሚለው የህገ-መንግስቱ መግቢያ ላይ የጨቋኝ

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) የፖለቲካ ፕሮግራም ሰነድ | AFPO’s Manifesto

7
ተጨቋኝ ትርክትን ያዘለ፣ አማራን ቅኝ ገዥና ጨቋኝ በማድረግ ለህልውና ስጋት አደጋና ዘር መጥፋት (genocide)
ያጋለጠ ስለሆነ፣
3ኛ. በህገ-መንግስቱ አንቀፅ 8 ከቁ(1-3) የሕዝብ ሉዓላዊነት፣ ስልጣንና ተሳትፎ “ለብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች”
ብቻ የሰጠና የክልል ስያሜ ካገኘው ብሄር ውጭ ያሉትን ብሄረሰቦችና ዜጎች ሀገር አልባ ያደረገ ስለሆነ፣
4ኛ. በህገ-መንግሥት አንቀጽ 39(1)፣ 46(2) እና 49(5) በቅደም ተከተል፡
ሀ. መገንጠል ገደብ የሌለው መብት ስለመሆኑ፣
ለ. ክልሎች የተዋቀሩበት መስፈርቶች (የሕዝብ አሰፋፈር፣ቋንቋ፣ማንነትና ፈቃድ) ሀገርን የመበታተን
አደጋ ስለሆኑ፣
ሐ. አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሀል ስለሚገኝ ለኦሮሚያ ልዩ ጥቅም እንደሚገባ ተደርጎ መቀመጡ. . .
የሚሉ አንቀፆች የአማራን ታሪካዊና ህጋዊ ባለቤትነት ግምት ውስጥ ባለማስገባቱ እና የአማራን ማንነትና
ህልውና የሚፈታተን ከመሆኑም በላይ ተገንጣይ ኃይሎች የአማራን አጽመ-ርስት ህገ-መንግስታዊ ሽፋን
በመስጠት ገንጥሎ ለመውሰድ የታሰበ መሆኑ፣ ይህንም ውሎ ሲያድር ተግራዊ ለማድረግ እየሰሩ መሆኑ፣
5ኛ. መሰረታዊ የሆኑ ዓለም አቀፍ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ከሆኑት ውጭ ያሉት በርካታ አንቀፆች
የአማራን ሕዝብ ለህልውና አደጋ ያጋለጡ ስለሆኑ፣
ከህገ-መንግስቱ በተጨማሪ በዚሁ መሰረት የወጡ የክልል ህገ-መንግስቶች፣ አዋጆችና ደንቦችም አብዛኞቹ አማራን
ያገለሉ ከመሆናቸውም በላይ እነዚህን በመጠቀም የአገዛዙ መዋቅር እስከታች ድረስ ተግባብቶ አጠቃላይ የአማራን
ሕዝብ በማጥፋት ላይ ይገኛል።
በመሆኑም ይህ ህገ-መንግሥት ታግዶ በምትኩ አዲስ ህገ-መንግሥት እስኪፀድቅ ድረስ የሽግግር ቻርተር ተቋቁሞ
ይቆያል፡፡ ይህ ማለት በህገ-መንግስቱ መሰረት ከዚህ በፊት የወጡ አግላይና አድሏዊ የሆኑ መመሪያዎችና ደንቦች
በሙሉ እውቅና አይኖራቸውም፡፡ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ሀቀኛ ወኪሎቻቸውን በተዓማኒ ሂደት መርጠው
ሙሉ ተሳትፎ የሚደረግበትና አለማቀፍ አሰራርን በተከተለ መልኩ አዲስ ህገ-መንግስት እንዲሁም ከህገ-መንግስቱ
የሚቀዱ ህጎችና አሰራሮች ስራ ላይ እንዲውሉ ይደረጋል፡፡
4ኛ. ትክክለኛ የሆነ የሕዝብ ቆጠራ ማካሄድና የበጀት ቀመር ማሻሻያ ማድረግ
የአማራ ሕዝብ ቁጥር ፀረ-አማራ በሆነው በራሱ በመንግሥት ሪፖርት ሳይቀር በአስደንጋጭ ሁኔታ እያሽቆለቆለ መሆኑ
ተገልጿል፡፡ ከዚህ በፊትም በ1999 ዓ.ም በነበረ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ በምክር ቤት በቀረበ ሪፖርት 2.4 ሚሊዮን አማራ
እንደተራ ነገር ጠፋ ተብሎ ምንም ምርመራ ሳይደረግበት የአንድ ሰሞን አጀንዳ ሆኖ መቅረቱ የአማራ ሕዝብ ምን ያክል
የህልውና አደጋ እንደተጋረጠበትና የጀመርነው ትግል ምን ያክል ፍትኃዊ መሆኑንም ጭምር ያረጋግጣል።
ይህ በድንገት በወጣ ሪፖርት ይገለጽ እንጅ ከዚህ ቆጠራ በኋላም ያለምንም ማቋረጥ የአማራን የጅምላ ሞትና ቀብር
መስማት የተለመደ የዕለት ከዕለት ዜና ሆኖ ቀጥሏል። የአማራ ሕዝብ በአገዛዙ ሪፖርት በየጊዜው ያሽቆለቆለበት ሁኔታ
ከዚህ በታች ባሉት ዋና ዋና ምክንያቶች እንደሆነ ይታመናል፡-

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) የፖለቲካ ፕሮግራም ሰነድ | AFPO’s Manifesto

8

  1. ፀረ-አማራ በሆነው በአገዛዙ ሴራ ቁጥሩ ሆን ተብሎ በቆጠራ ወይንም በሪፖርት እንዲቀነስ በመደረጉ፣
  2. ከክልሉ ውጭ ያለው አማራ በየዕለቱ በማንነቱ በሚደርስበት ሰቆቃ ምክንያት በስጋት ማንነቱን ለመግለጽ
    በመቸገሩ፣
  3. አማራው በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል በጅምላ በመገደሉና በመሰደዱ፣
  4. ከላይ ባሉት በሶስቱም ምክንያቶች ወይንም በሌሎች ወደፊት ዝርዝር ጥናት በሚጠይቁ ምክንያቶች ሊሆን
    ይችላል።
    ስለሆነም አፋሕድ በመላ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚገኙ አማራዎች እና የአማራ ተወላጆች ትክክለኛ ቁጥራቸዉ፤ እንዲሁም
    ተዓማኒ የሕዝብ ስርጭት እና ስብጥር ይፋ እንዲደረግ፤ የአማራ ሕዝብ ቁጥር ሆን ተብሎ የተቀነሰበትን ምክንያት
    እንዲጣራ ይደረጋል። በተጨማሪም በመንግስታዊ ሴራ ምክንያት የዚህ ሕዝብ ቁጥር በመቀነሱ ምክንያት በየአመቱ
    ሊያገኘው የሚገባውን ነገር ግን የተነፈገውን በጀትና በዚህ ምክንያት ያጣውን ልማትና እድገት ማካካሻ እንዲያገኝ
    ይደረጋል፡፡
    5ኛ. የሀሰት ትርክትን ማረምና ገዥ ብሄራዊ ትርክት ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ
    አማራ ክፉኛ የተጎዳበት ተገንጣይ ኃይሎች በፈጠሩት የተዛባ ትርክት ነው፡፡ ድርጅታችን ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ላይ
    ሀገራዊ (ብሔራዊ) ገዥ ትርክት አለ ብሎ አያምንም:: ይልቁንም ጎሳዊ እና ተነጻጻሪ የሀሰት ትርክቶች ይበልጥ በስፋት
    የሚስተዋሉበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን፡፡ ይህ ደግሞ ሀገርን ያፈርሳል::
    በመሆኑም ትርክትን በተመለከተ በሁሉም ዘንድ ቅቡልነት ያለው ጠንካራ የሆነ ተነጻጻሪ ትርክት ማቅረብና ሌሎች
    አግላይና ጎጅ ትርክቶችን በማስተካከል ገዥ ሐገራዊ ትርክት እንዲፈጠር አፋሕድ የበኩሉን ሚና ይወጣል።
    6ኛ. የወሰን እና ማንነት ጥያቄዎችን በተገቢው መመለስ
    ታሪክ በግልፅ እንደሚያስቀምጠው አማራው የበዛ ዋጋ እየከፈለ አስከብሯቸው የኖሩት አጽመ-ርስት የነበሩት ቦታዎች
    እጅግ ሰፊ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ባሳለፍናቸው የታሪክ ጉዞዎች አማራ እንደሌሎች በብሄር ማንነት ታጥሮ ታላቁን
    የአማራ ሀገር ከመመስረት ይልቅ ከተለያዩ ቦታዎች የመጡትን በሰላም ተቀብሎ ከሁሉም ጋር በፍቅርና በመከባበር የቆየ
    ሕዝብ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ነገር ግን ያለምንም ህጋዊ መሰረትና ያለ አማራው ተሳትፎ ኢሕአዴግ ቆርሶ ከሰጠው ክልል
    ውጭ የሚኖረው አማራ ዋጋ ከፍሎ ዘመን ባሻገራት ሀገሩ እንደመጤ ተቆጥሮ ተሳዳጅና ተፈናቃይ እንዲሆን ተፈርዶበት
    ከግማሽ ክፍለ-ዘመን በላይ በየሄደበት እንዲገደልና እንዲፈናቀል ተደርጓል፡፡
    ይህን አደጋ ለመቀልበስ በህዝቦች መልካም ፈቃድ (consent of the people) ላይ የተመሰረተ እና ማንነትን፤ ታሪክን እና
    መልክዓ-ምድርን መሰረት ያደረገ ፌደራላዊ ስርዓት መገንባት ያስፈልጋል። አዲሱ የፌደራሊዝም አወቃቀር በሚከተሉት
    መንገዶች የወሰን፣ የአስተዳደርና ማንነት ጥያቄዎችን መመለስ ይቻላል፡፡
    ሀ. የወሰን ተዛምዶ/ኩታ ገጠም ለሆኑት
    በጉልበትና በተሳሳተ አሰራር (ከመልክዓ-ምድር፣ከባህልና ከታሪክ ባልተዛመደ ሁኔታ) ከቅርብ ወገናቸው
    በመገንጠል ወደ ሌሎች አጎራባች ክልሎች በማይመስላቸው መንገድ ተካለው የነበሩና ከፍተኛ የሆነ በደል

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) የፖለቲካ ፕሮግራም ሰነድ | AFPO’s Manifesto

9
ሲደርስባቸው የኖሩት አማራዎች በጥናት ላይ በመመስረትና በህዝቦች ነፃ ፈቃድ የመልክዓ-ምድር፣ የባህልና ታሪክ
አምሳያ ወደሆኑበት አስተዳደር እንዲካለሉ ይደረጋል።
ለ. መልክዓ ምድራዊ ትስስር የሌላቸውን በተመለከተ
እስካሁን ድረስ በማንነታቸው ለደረሰባቸው ጉዳት ከላይ በ2ኛ ተራ ቁጥር በተቀመጠው መሰረት ፍትሕ እንዲያገኙ
የሚደረግ ሲሆን ዘላቂ ፍትሕና ሰላምን ለማረጋገጥ ግን ወደፊት በሚኖረው ፌደራሊዝም አወቃቀር መሰረት
እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁሉ በአካባቢው ባለው አስተዳደር በማንነታቸው ምክንያት ምንም አይነት
አድሎ ሳይደርስባቸው እኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡
7ኛ. የእኩል ተጠቃሚነት እና በጸጋው ልክ መልማት
አማራ በደረሰበት ፖለቲካዊ ሸፍጥ የምድራችን ድሀ ሕዝብ እንዲሆን ተደርጓል:: ይህ ገናና ሕዝብ ለዚህ ውርደት የበቃው
ደግሞ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ በደረሰበት ስልታዊና መዋቅራዊ በደል ነው:: ህዝባችን አሁንም በባዶ እግሩ የሚሄድ፤
አሁንም በበሬ የሚያርስ፤ የንፁህ መጠጥ ዉሀ ቅንጦት የሆነበት፤ የተማሩ ልጆቹ ሥራ የማያገኙበት ሕዝብ ሆኗል፡፡
አማራው ከራሱ አልፎ ለሌሎችም መትረፍ የሚችል እጅግ እምቅ የተፈጥሮ ሀብት፣ ሰፊና ለም መሬት፣ አመቱን በሙሉ
የሚፈሱ ወንዞች፣ ሃይቆች፣ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ የቱሪስት ማዕከላት እንዲሁም ሰፊ የሰው ሃብት ባለቤት ቢሆንም
አገዛዞቹ በፈጠሩት አድሏዊ አሰራርና የኢኮኖሚ ሸፍጥ ምክንያት እስካሁን ድረስ የልማት ተጠቃሚ ሊሆን አልቻለም።
በመሆኑም በቀጣይ ይህን ኢ-ፍትሃዊ አሰራር ተስተካክሎ ከዚህ በፊት የደረሰበትን ኪሳራ ሊያካክስ የሚችል በመልማት
ፀጋው ልክ እንዲለማ በጥናት ላይ የተመሰረተ የኢኮኖሚ ማሻሻያ እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) የፖለቲካ ፕሮግራም ሰነድ | AFPO’s Manifesto

10

ምዕራፍ ሁለት

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ቁልፍ መርሆዎች

2.1 የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነትን ማስጠበቅ
የኢትዮጵያ የግዛት አንድነት፣ ሉዓላዊነትና፣ ብሔራዊ ጥቅም ሳይሸራረፍ መጠበቅ እንዳለበት ድርጅታችን በፅኑ ያምናል።
የሀገር ማንነትና መገለጫ የሆኑ የሕዝብ እሴቶች በአግባቡ መጠበቅ እንዳለባቸውም በጽኑ ያምናል ለዚህም ተግቶ ይሰራል።
ዜጎች ከማንኛውም የውስጥና የውጭ ወራሪ አደጋ ውስጥ እንዳይወድቁ አስተማማኝ የሆነ የፀጥታ መዋቅር እንዲዘረጋ
ያደርጋል፡፡
2.2 እኩልነትና ነፃነት
የአማራ ሕዝብ ለነፃነት ቀናዒ ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ህዝቦች ጋር ተከባብሮ መኖር የሚወድ የእኩልነት ተምሳሌት ሕዝብ
ነው:: ከዚህ እሴት በመነሳት ለሁሉም እኩል የሆነች ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች ተከባብረውና ተሳስበው የሚኖሩባት ሃገር
መኖር ለዘላቂ ሰላምና ልማት ወሳኝ መሆኑን ድርጅታችን በፅኑ ያምናል፡፡ በሀገራችን ያሉ ጎሳዎች፣ ሃይማኖቶች፣ ቋንቋዎች
እና ባህሎች የሁላችንም እንደመሆናቸው መጠን ተገቢው እውቅናና እንክብካቤ ሊደረግላቸው እንደሚገባ አፋሕድ በጽኑ
ያምናል።
2.3 የሃይማኖትና የመንግሥት መለያየት
መንግስታዊ ሃይማኖት አይኖርም፡፡ ሃይማኖታዊ መንግሥትም አይኖርም፡፡ መንግሥት በሃይማኖት አሰራር ጣልቃ አይገባም፤
ሀይማኖትም በመንግሥት አሰራር ጣልቃ አይገባም፡፡
2.4 በትብብር መሥራት
የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት ወጥ አማራዊ ተቋም እንዲፈጠር አጥብቆ ይሰራል። በተጨማሪም ከማንኛውም ጭቆናንና ዘር
ጭፍጨፋን ከሚቃወም ፍትሕ ፈላጊ ፖለቲካዊ ድርጅት ጋር ተባብሮ የመሥራት ጽኑ ፍላጎት አለው። ድርጅታችን ከሁሉም
ጭቁን ሕዝብ ጎን ቆሞ የሚታግል ድርጅት ሲሆን ወደፊት ሀገራዊ መንግሥት ለማቋቋምና የዜጎችን እኩልነት ለማስፈን
በትብብር የሚሰራ ይሆናል፡፡

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) የፖለቲካ ፕሮግራም ሰነድ | AFPO’s Manifesto

11

ምዕራፍ ሶስት

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ፕሮግራሞች

3.1 የፖለቲካ ፕሮግራም
የአማራ ሕዝብ በተከታታይ የአገዛዙን ወንበር በተቆናጠጡ ፀረ-አማራ ኃይሎች ፖለቲካዊ ሸፍጥና ክህደት ተፈጽሞበታል::
በባህሉ፣ በእሴቱ፣ በክብሩና በታሪኩ ሁሉ ጥቃትና ማጥላላት ተፈፅሞበታል፤በማንነቱ ምክንያት የዘር ፍጅት ተካሂዶበታል::
ይህ በቅድሚያ ብሄራዊ እውቅና የሚሠጠው ሆኖ ዘላቂ መፍትሄ የሚሻ ይሆናል:: በአንድ በኩል የደረሰበትን ቁስል
ለማድረቅ በሌላ በኩል ከሌሎች ህዝቦች ጋር ያለውን ሰላማዊ ግንኙነት ለማስቀጠል ጉዳዩን በጥንቃቄ ማከም ያስፈልጋል::
በመሆኑም የአማራ ሕዝብ የደረሰበትን ጥቃትና ዘር ፍጅት አክሞ ወደ ሽግግር ፍትሕ የሚወስድ ከሌሎች በተመሳሳይ ሂደት
ካለፉ ሀገሮች ልምድ በመቅሰም የኢትዮጵያ እውነት አፈላላጊና እርቅ ኮሚሽን ይቋቋማል:: በጥናት የተመሠረተ ገዥ ትርክት፣
ፍትሕ እና ብሄራዊ እርቅ እንዲመጣ ይደረጋል::
3.1.1 ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታና የሰብዓዊ መብቶች መከበር
በሁሉም አሰራሮች ውስጥ የህግ የበላይነትን በማስፈን፤ የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ልምምድ በማድረግ
ዲሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች ይከበራሉ፡፡ ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸውና ያፀደቀቻቸው ዓለም-አቀፋዊና አህጉራዊ ሕጎችና
ድንጋጌዎች እንደነባራዊ ሁኔታው እየታዩ ተቀባይነት ይኖራቸዋል፡፡ አገሪቱ በተለያዩ ወቅቶች የተቀበለቻቸው እና
ያወጣቻቸው ሕጎች የዜጎችን መብት ይጥሳሉ ወይም ይገድባሉ ተብለው ከታመነባቸው ሊሻሻሉ ወይም ከእነአካቴው
ሊሰረዙ ይችላሉ፡፡ ዜጎች ሃሳባቸውን በነጻነት ያለገደብ የመግለጽ መብታቸው እንዲከበር ይደረጋል፡፡ የተለያዩ የሲቪክ
አደረጃጀቶች እንዲቋቋሙና እንዲጠናከሩ ይደረጋል፡፡ ሕፃናትንና ሴቶችን በተመለከተ ከዓለምአቀፍ ሕጎች በተጨማሪ
አገራዊ ነባራዊ ሁኔታውን ያገናዘበ ሕግ እንዲወጣ ይደረጋል፡፡
3.1.2 የመንግሥት ስልጣን አወቃቀር
ኢትዮጵያ ውስጥ በአንድነትና በብዝኃነት (Unity vs Diversity) መካከል ከፍተኛ ውጥረት እንደነገሰ ይታወቃል::
አንዳንዶች ከብዝኃነት ይልቅ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ ብቻ ትኩረት እንዲሰጥ የሚፈልጉ እንዲሁም አወቃቀሩ ለዚሁ
በሚጠቅም መልኩ እንዲሆን ይፈልጋሉ:: ሌሎች ደግሞ በማንነት ላይ ትኩረት እንዲደረግና እስከ መገንጠል በመሄድ
የኢትዮጵያን መቀጠል የሚፈታተን ፍላጎት ያላቸውም አሉ::
ድርጅታችን ከአማራ ሕዝብ ታሪክና እሴት እንዲሁም ከነባራዊ ሁኔታ በመነሳት ቀጣዩ የመንግሥት አወቃቀር የኢትዮጵያን
መቀጠልና የማንነት ፍላጎቶች የሚታረቁበትን አውድ ለመፍጠር ይሰራል:: አማራው አማራነቱ (የብሄር ማንነቱ)፣
ኢትዮጵያዊነቱ (የዜግነት ማንነቱ) ተጋጭቶበት አያውቅም።

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) የፖለቲካ ፕሮግራም ሰነድ | AFPO’s Manifesto

12
ከዚህ በተጨማሪ የመንግሥት አወቃቀሩን በተመለከተ በቀጣይ ሀገር ምስረታ ላይ በሚደረጉ ሁሉን አሳታፊ ዉይይቶች
የሚወሰን ይሆናል፡፡ ሆኖም ድርጅታችን ሀገራዊ አንድነትን በሚያጎሉ እና ከመነጣጠል ይልቅ በመተሳሰብ፣ ሀገራዊ ማንነት
ላይ ትኩረት ቢሰጥ እኩልነትና ፍትህ እንዲሁም ዘላቂ ሰላምንና አንድነትን እናመጣለን የሚል እምነት አለው፡፡ ለዚህም
ስኬት ሲባል ሁሉም ዜጋ በሀገሩ የሚኮራበትና በየትኛውም ቦታ ያለስጋት ሰርቶ የሚከብርበትና እኩል ተወዳዳሪ የሚሆንበት
ሂደታዊ የፌደራላዊ ስርዓት አወቃቀር እንዲኖር አማራጭ ሃሳብ ይዞ ይቀርባል፡፡
በተለይ አፋሕድ በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ትኩርት አድርጎ ይሰራል።
ሀ/ የአማራ ሕዝብ ብሎም የኢትዮጵያ ሕዝብ ተራማጅና የስልጣኔ ባለቤት እንደመሆኑ መጠን ባህሉን፣ ሃይማኖቱን
እና እሴቱን ጠብቆ የዘመናዊው ዓለም ከሚራመድበት ሁለንተናዊ እድገት ጋር የሚጣጣም ርዕዮተ-ዓለም
(Ideology) ጠቃሚ እንደሆነ ይገነዘባል፡፡ ስለሆነም ተራማጅ የሆነ ነገር ግን የሺህ ዘመን እሴትን የሚጠብቅ
ፕራግማቲዝም (pragmatism) ርዕዮተ-አለም ይከተላል፡፡
ለ/ የአገር አስተዳደር መዋቅሩ ሂደታዊ ፌደራላዊ ሥርዓትን የተከተለ ይሆናል፡፡ የፌዴራሉ አስተዳደር ግዛቶች
ሲዋቀሩ ለልማትና ለአስተዳደር አመቺነትን፤ የሕዝብ አሰፋፈርንና ፍላጎትን፤ የታሪክና የስነ-ልቦና ትስስርን፣
የመልክዓ-ምድር አቀማመጥን መሰረት ማድረግ እንደተጠበቀ ሆኖ ሁሉን አሳታፊ በሆነ ውይይት የሚወሰን
ይሆናል።
ሐ/ የፌደራል መንግስቱና የፌደራል መንግስቱ አባላት (ክፍለ-ሀገሮች) ተለይቶ የሚሰጣቸው ሥልጣንና ሃላፊነት
በሕግ ይወሰናል፡፡
መ/ አማርኛ የሀገሪቱ ብሔራዊና የሥራ ቋንቋ ሆኖ ይቀጥላል፡፡
ሠ/ ግዛቶች እና ከተማ አስተዳደሮች በሚያስገቡት ገቢ መጠን ከሚመደብላቸው በጀት በተጨማሪ ዕድገታቸውን
ለማፋጠን ሲባል እንዳስፈላጊነቱ የፌደራሉ መንግሥት ፍትኃዊ በጀት ይመደብላቸዋል፡፡
ረ/ የፌደራል መንግስቱ ሦስት የሥልጣን አካላት ይኖሩታል፡፡ እነሱም ሕግ አውጭ፤ ሕግ ተርጓሚና ሕግ አስፈጻሚ
ናቸው፡፡ እነዚህ የሥልጣን አካላት አንዱ ከሌላው ገለልተኛ እና የየራሳቸው የሥራ ድርሻ ኖሯቸው አንዱ ሌላውን
እንዲቆጣጠር (check and balance) ተደርገው ይዋቀራሉ፡፡ ይህ የፌዴራሉ መንግሥት አወቃቀር በፌዴራሉ
አባል ግዛቶችም በተመሳሳይ መልኩ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
ሰ/ የፖለቲካ ሥርዓቱ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓትን የተከተለ ይሆናል፡፡ የምርጫ ሥርዓቱ ደግሞ ተመጣጣኝ
(proportional) ይሆናል። መንግሥታዊ ሥርዓቱም በሂደት ወደ ፕሬዚዳንታዊ ሥርዓት ይሸጋገራል፡፡
3.1.3 የውጭ ግንኙነት
የውጭ ግንኙነት መርሃችን የአገርና ሕዝብን ዘላቂ ጥቅምን መሰረት ያደረገ ይሆናል። ከዚህ በተቃራኒ የተደረጉ የውጭ
ግንኙነት ውሎችና ስምምነቶች ሕጉን መሰረት ባደረገ መልኩ ሊሻሻሉ ወይም ፈፅሞ ሊሰረዙ ይችላሉ፡፡ በውጭ ሀገራት
የሚኖሩ ዜጎች ክብራቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ ያላሰለሰ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ይደረጋል፡፡

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) የፖለቲካ ፕሮግራም ሰነድ | AFPO’s Manifesto

13

3.1.4 የሽግግር ጊዜ
ከድል ማግስት፣ የኢትዮጵያን ሀገረ መንግሥት ቅርፅና አወቃቀር እንዲሁም ስልጣን ለመወሰን ሁሉን አቀፍና አካታች
ዉይይት ይደረጋል፡፡ በዚህ ዉይይት ሁሉም ህዝቦች በእኩልነትና ትርጉም ባለዉ ዉክልና እንዲሳተፉ ይደረጋል፡፡
ብሔራዊ እርቅንና አካታች የሀገር ምስረታን ለመተግበር ያስችል ዘንድ ልዩ ልዩ ምሁራንና ባለሙያዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣
ሴቶች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ ሲቪክ ማህበራት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የነፃነት ታጋዮች፣ ብሄረሰቦችና ሌሎችም ጭምር
የተካተቱበት ከችግሩ ምንጭ አስከ መፍትሄው ድረስ በሚደረግ ሀገራዊ ውይይትና ምክክር ከተፃራሪ ትርክቶች ይልቅ ገዥ
የሆነ ሀገራዊ ትርክት እንዲፈጠርና የጋራ እጣ ፈንታም እንዲኖረን የሽግግር ምክረ ሃሳብ ይቀርባል። እነዚህ ውይይቶች
በማንነት ላይ የተፈፀሙ ወንጀሎችና የዘር ፍጅቶች እንዲሁም ስልታዊ ጥቃቶች እዉቅናና የሽግግር ፍትሕ (Transitional
Justice) አግኝተው የጥላቻና የመጠራጠር ዘመን አብቅቶ የእኩልነት፣ የአንድነትና የመተሳሰብ ዘመን እንዲመጣ አስቻይ
ሁኔታዎችን እንደሚፈጥሩ ይታመናል፡፡ በተለይም የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ህወሓትና የኦህዴድ ብልጽግና የተከተሉትን
የማንነት ፖለቲካ፤ የሀገርን አንድነት ሊያስጠብቅ በሚችል ሁሉም ሰው በዜግነቱ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቱ ሊከበርለት
በሚያስችል ስርዓት በሂደት መተካት እንደሚገባው ፅኑ አቋም አለው። በዚህም ሂደት ጠንካራ አገራዊ እንድነት
ከመፈጠሩም በላይ የሰላም አየር ወደ ሁሉም አጎራባች ሀገራት እንዲነፍስ ለማድረግ ትልቅ ተስፋን ይዞ እንደሚመጣ
ያምናል፡፡
3.2 የኢኮኖሚ ፕሮግራሞች
የአማራ ሕዝብ በደረሰበት መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ጥቃት ምክንያት የምድራችንም የሀገራችንም ድሃ ሕዝብ እንዲሆን
ተደርጓል:: የአማራ ሕዝብ በተለይ ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ በህወኃት መሩ የኢሕአዴግ አገዛዝ ከደረሰበት ስርዓታዊ ጥቃት
በተጨማሪ ጥገናዊ የፖለቲካ ለውጥ ከመጣበት ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በኦህዴድ መሩ ብልጽግና አገዛዝ አስከፊ ጦርነት
ተከፍቶበት ከባድ የሆነ ሰብዓዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ውድመት እየደረሰበት ይገኛል:: አብዛኞቹ መሰረተ-ልማቶች
ወድመውበት ምንም አይነት ጥገና ሳይደረግላቸው ቀርተዋል፣ አሁንም መሰረተ ልማቶች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ
እየወደሙ ይገኛሉ:: ስለሆነም በጦርነት ለደረሰበት ጉዳትና ስርዓታዊ ጥቃት ልዩ የኢኮኖሚ ማካካሻ ፕሮግራም እንዲኖረው
ይደረጋል::
3.2.1 የመሬት ባለቤትነት
ለአማራ ሕዝብ መሬት ለብዙ ሺህ ዓመታት በርስት ሲያስተላልፈው የቆየ ቋሚ ኃብት ብቻ ሳይሆን ማንነቱም ጭምር ነው።
ይሁን እንጅ ከ1960ዎቹ መጨረሻ ጀምሮ አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ከመሬቱና ርስቱ “ሰፋሪ”፣
“ወራሪ”፣ “ተስፋፊ”፣ “መጤ” ወዘተ የመሳሰሉ የሀሰት ስያሜዎች እየተሰጠው እንዲፈናቀል ተደርጓል፤ ያለአግባብ መሬቱና
ርዕስቱ ተወስዶበታል:: በመሆኑም ይህን የሚያጠና የእውነትና የእርቅ ኮሚሽን ይቋቋማል:: ኮሚሽኑም ከበቂ ጥናት በኋላ
አማራን ለማፈናቀል የወጡ ህጎችን በመሻር አዲስ ሚዛናዊ ህግ እንዲወጣ ይደረጋል። እንዲሁም የይዞታ መረጃ በማጣራት
ፍትሃዊ የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል።

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) የፖለቲካ ፕሮግራም ሰነድ | AFPO’s Manifesto

14
የመሬት ይዞታ የግለሰብ፤ የመንግሥት ፣ የእምነት ተቋማትና የኅብረተሰብ በሚል በአራት አካላት ሥር እንዲሆን ይደረጋል፡፡
ይህን በማይጣረስ መልኩ የገጠርም ይሁን የከተማን የግል ይዞታ፣ መሬት መሸጥና መለወጥን፣ በባንክ መበደር፣ እንዲሁም
ለሦስተኛ አካል በውርስ ማስተላለፍ ይቻላል፡፡
የመንግሥት የምንላቸው መሬቶች የመንግስታዊ ተቋማት ቦታዎች፣ ጥብቅ ደኖችና ፓርኮች ይሆናሉ፡፡ እነዚህ መሬቶች
በመንግሥት ይዞታ ውስጥ ሆነው ለሕዝብ ጠቀሜታ የሚውሉ ይሆናሉ።
የአርብቶ አደር የግጦሽ ቦታዎች እና ባህላዊ ተግባራትን ለማከናወን የሚውሉ ቦታዎች፣ ለማኅበራዊ አገልግሎት የሚውሉ
ቦታዎች የወል መሬቶች ሲሆኑ ባለቤትነታቸው የኅብረተሰቡ ይሆናል፡፡
የቤተ እምነት ቦታዎች እና ለማንኛውም ሃይማኖታዊ ክንውኖች የሚውሉ መሬቶች በኃይማኖቱ ተከታዮች ሥር ይሆናሉ።
3.2.2 ግብርና
ግብርና ለአማራና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ዋነኛ የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ ስለሆነም ድርጅታችን የግብርና
ስርዓቱን በማዘመንና መዋቅራዊ ሽግግር በመፍጠር ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ይሰጣል፡፡ የመሬትን ለምነት
ለማሻሻል ወይንም ጠብቆ ለማቆየት አስፈላጊ የሆኑ ፕሮግራሞች ተነድፈው ሥራ ላይ እንዲውሉ ይደረጋል፡፡
3.2.3 ኢንዱስትሪ
የአማራ ሕዝብ በኢንዱስትሪ መሰረተ ልማቶች ጭራ ተብሎ የሚገለፅ ነው፡፡ የኢሕአዴግም ሆነ የብልጽግና ስርዓት ለአማራ
ሕዝብ ሊጠቅም የሚችል ከመጠጥ ፋብሪካ ወይንም ከኢንዱስትሪ ሸድና ጥቃቅን ፋብሪካዎች ያለፈ ይህ ነው የሚባል ተቋም
አልገነባለትም፡፡ በመሆኑም ይህን ታሪክ ሊቀይር የሚችል ግብርናውን የሚያግዙና ተመጋጋቢ የሆኑ፤ ለወጣቶች የሥራ
እድል የሚፈጥሩ፤ ከተሜነትን የሚያመጡ የኢንዱስትሪ አማራጮች እየተገመገሙ በጥናት ይገነባሉ፡፡
የአማራ ሕዝብ አኗኗር በግብርና ላይ የተመሰረተ ከመሆኑ አንፃር ግብርናውን የሚያዘምኑ እና ለግብርናው ግብዓት የሚሆኑ
ብሎም ከግብርናው ግብዓት በሚቀበሉ ኢንዱስትሪዎች ላይ በዋናነት ትኩረት ተደርጎ ይሰራል፡፡ ኢንዱስትሪው የገቢ
ምርቶችንና ጥሬ ዕቃዎችን የሚተካ እንዲሆን ይበረታታል፡፡
ገበሬዎችን በፈቃዳቸው በማህበራትና በኅብረት ሥራ ማኅበራት በማደራጀት የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ
ኢንዱስትሪዎችን እንዲያቋቁሙ መንግሥት ልዩ እገዛ ያደርጋል፡፡ ለአጠቃላይ አገራዊ ዕድገት አዋጭ የሆኑ ዘርፎች
ተለይተው በዘርፉ ለሚሰማሩ ባለሐብቶች የግብር እፎይታ ጊዜን ጨምሮ ከቀረጥ ነፃ የሆነ አሰራር ይተገበራል፡፡
በውጭ አገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በኢንዱስትሪ ግንባታው እንዲሳተፉ ለማበረታታት ሲባል ልዩ እገዛ
ይደረግላቸዋል፡፡
ለወጣቶች የሥራ እድል ለመፍጠርና ብዙ የሰው ኃይል ሊያሳትፉ የሚችሉ ትንንሽ ኢንዱስትሪዎችን ለማበረታት የገንዘብ
ብድርን ጨምሮ የመስሪያ ቦታና የግብር እፎይታ ጊዜ እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡
በተጨማሪም ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላቸው የረቀቀ ቴክኖሎጂና ከፍተኛ ካፒታልን የማይጠይቁ እንዲሁም የኢትዮጵያን
ተፈጥሮአዊ ጸጋዎች በቀላላሉ የሚጠቀሙ ልዩ የኢንዱስትሪ ተቋማት እንዲመሰረቱ ድጋፍ ይደረጋል፡፡

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) የፖለቲካ ፕሮግራም ሰነድ | AFPO’s Manifesto

15

3.2.4 ንግድ
የንግድ ስርዓቱ ነፃና ፍትሃዊነትን የሚያበረታታ ሆኖ ይዘረጋል፡፡ የንግድ ስርዓቱ የሕዝብን እና የሀገርን ጥቅም ያማከለ፣ የግል
ክፍለ-ኢኮኖሚ-ተኮር የነፃ ገበያ ስርዓትን የሚያበረታታና የገበያ ተወዳዳሪነትን የሚፈጥር እንዲሆን ይደረጋል፡፡ ሆኖም
በተመረጡና ሕዝብን የተሻለ ተጠቃሚ በሚያደርጉ የንግድ ዘርፎች እና አገልግሎቶች ወይንም የሀገርን እሴት መጠበቅ
ቅድሚያ የሚሰጠው ሆኖ ሲገኝ መንግሥት ጣልቃ የሚገባ ይሆናል፡፡
3.2.5 መሰረተ ልማቶች
ድርጅታችን መሰረተ ልማቶች የዕድገት ማስፈንጠሪያዎች ናቸው ብሎ ያምናል፡፡ በመሆኑም የመንገድ፣ የስልክ፣ የመብራት፣
የንፁህ መጠጥ ውኃ ግንባታዎች፣ የኢንተርኔት፣ ሌሎች መገናኛ ዘዴዎችና መሰል መሰረተ ልማቶች ከመንግሥት በተጨማሪ
በግሉ ባለሐብቶች እንዲቀርቡ ይደረጋል፡፡ የኅብረተሰቡን ንቃተ ኅሊና ለማሳደግ በእነዚህ ልማቶች ላይ እንዲሳተፍ
ይደረጋል፡፡ የአየር፣ የውኃ፣ የየብስና የባቡር መጓጓዣ ዘዴዎች ዘመኑን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ይገነባሉ፡፡ የኢንዱስትሪ ክፍለ
ኤኮኖሚውም ለዚህ ዘርፍ ግብዓቶች ማቅረብ እንዲችል ልዩ እገዛዎች ይደረጉለታል።
3.2.6 የውኃ ሐብት
ሀገራችን ያላት የዉሃ ሃብት በመጭዉ ጊዜ ተፈላጊነታችንን እንደሚጨምረዉ ይታመናል፡፡ የውኃ አካላት ለሕዝብ ዕድገትና
ዘመናዊ አኗኗር ያላቸው ወሳኝነት ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ በመንግሥትም ሆነ በግሉ ክፍለ-ኢኮኖሚ ለልማት
እንዲውሉ ይደረጋል፡፡
3.2.7 የቱሪዝም ሃብት
የአማራ ሕዝብ አስደናቂ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ የቱሪዝም መስህቦች ባለቤት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ለዓለም ኃብት ይበቁ ዘንድ
ካስመዘገበቻቸው የተለያዩ ቅርሶች ውስጥ እጅግ አስደናቂዎቹ በአማራ ሕዝብ ግዛት የሚገኙት ናቸው፡፡
የአማራ ግዛት ‹‹የታሪክ የጉዞ መስመር›› በመባል የሚታወቀውን በብዛት በመሸፈን ‹‹በዓለም ዘንድ ለሚደነቁት የኢትዮጵያ
ቅርሶች እምብርት (The Heart Land of Ethiopian World Wonders)›› የሆኑ አማራ ለኢትዮጵያ ሞገስነት ያበረከታቸው
ናቸው፡፡
በመሆኑም ድርጅታችን ከእነዚህም በተጨማሪ የሚገኙ ኃብቶችን በጥናትና በምርምር ፋይዳቸውን በማጎልበት፤ መሰረተ
ልማትም ባልደረሰባቸው መሰረተ ልማትን በመዘርጋትና ከአገልግሎት ሰጭዎች እይታ የራቁትን በማቅረብ ከፍ ያለ የቱሪዝም
ገቢ ምንጭነትን ለማጎልበትና የሕዝቡን ቀዳሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይተጋል፡፡
ከቱሪዝም አንፃር የአካባቢውን ነዋሪዎች ተጠቃሚ የሚያደርግ ስትራቴጂ ነድፎ ከመተግበር በተጨማሪ ለቅርሶች ጥበቃና
ክብካቤ እንዲሁም ለቱሪዝም መዳረሻዎች ልማት በመንግሥት በጀት እንዲደገፉ ይደረጋል፡፡

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) የፖለቲካ ፕሮግራም ሰነድ | AFPO’s Manifesto

16

3.3 ማህበራዊ ፕሮግራሞች
3.3.1 ትምህርት
ትምህርት የዕድገትና የሥልጣኔ መክፈቻ ቁልፍ ነው፡፡ ስለሆነም ማንኛውም ዜጋ ትምህርት የማግኘት እድልና ነፃነት
እንዲኖረው ይደረጋል፡፡ በሳይንስ እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ፣ ተወዳዳሪነትን የሚያመጣና ጥራቱን የጠበቀ የትምህርት
ሥርዓት እንዲኖር ይደረጋል፡፡ የትምህርት ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ መመዘኛውን ለሚያሟሉ የግል ባለሐብቶች
በትምህርት ኢንቨስትመንት ላይ እንዲሰማሩ ይደረጋል፡፡
ሥርዓተ ትምህርቱ ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ተላቆ በሙያው ባለቤቶች ብቻ እንዲመራ ይደረጋል፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ
ትምህርት በአፍ መፍቻ ቋንቋና በብሔራዊ ቋንቋ እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡ ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ትምህርቶች ልዩ ትኩረት
ይሰጣል፡፡ ልዩ ተሰጥዖ ያላቸውንና የላቀ ውጤት የሚያስመዘግቡ ተማሪዎችን የሚያበረታታ የልዩ ድጋፍ አሰራር ይዘረጋል፤
ከፍ ሲልም ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ይገነባሉ፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የቀደምት የእውቀትና የጥበብ ምንጭ የሆኑት የአብነት ትምህርት ቤቶችና መድረሳዎች ልዩ ትኩረት
ተደርጎ ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡ የቆየ ማንነታቸውን ለቀጣይ ትውልድ ያስተላልፉ ዘንድ አቅማቸው እየተገመገመ ወደ
ከፍተኛ የትምህርትና የምርምር ማዕከልነት ደረጃ ሊያድጉ የሚችሉበት አሰራር ይዘረጋል፡፡ እድሜ ጠገብ አዛውንቶች
በእድሜያቸው የቀሰሙትን እውቀት ለትውልዱ የሚያስተላልፉበት መንገድ በተለየ መልኩ ትኩረት ተሰጥቶት ይሰራበታል፡፡
አፋሕድ ሕጻናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ የሚያበረታታውን እና በዓለማቀፍ ደረጃ ቅቡልነት ያለውን አሠራር
ለመከተል ጽኑ እምነት እና ፍላጎት አለው። በዚህም መሠረት ሁኔታዎች ሲሟሉ በማንኛውም ክልል የሚኖሩ ዜጎች
ልጆቻቸውን በሚፈልጉት ቋንቋ እንዲማሩ ይደርጋል።
3.3.2 ጤና
ጤና የሰው ልጆች ሁሉ ሰብዓዊ መብት ነው፡፡ ስለሆነም ማንኛውም ሰው ለጤናው ምቹ በሆነ አካባቢ የመኖር መብት
አለው፡፡ የጤናው ዘርፍ በቅድሚያ በመከላከል መርህ ላይ ያተኮረ እንዲሆን ይደረጋል፡፡ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ድንገተኛ
የኅብረተሰብ ጤና አደጋዎችንና ወረርሽኞችን መመከት የሚያስችል የጤና ሥርዓት ይገነባል፤ የኅብረተሰብ ጤና አደጋዎች
ቅድመ ትንበያና መከላከል ሥራም ይሰራል፡፡ መሰረታዊ የጤና አገልግሎት ለሁሉም ማህበራሰብ ተደራሽ እንዲሆን
ይደረጋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የውጭ ሀገር እንግልትንና ወጭን መቀነስ በሚያስችል መልኩ ዘመናዊ ህክምናን በሀገር ውስጥ መስጠት
የሚቻልበት እድል እንዲኖር ዘመኑ ያፈራቸው ቴክኖሎጅዎችንና ከፍተኛ ባለሙያዎችን ያሟሉ የህክምና ተቋማትም
በየደረጃው እንዲኖሩ ይደረጋል፡፡ በውሉ ያልተጠኑ ነገር ግን ማህበረሰባችን ለዘመናት ሲጠቀምባቸው የኖሩ ልዩ ልዩ ባህላዊ
ህክምናዎች በተገቢው መንገድ እንዲጠኑ በማድረግ ጠቃሚ ሆነው ሲገኙ ከዘመናዊ ህክምና ጎን ለጎን አብረው እንዲሰጡና
እንዲዳብሩ ይደረጋል፡፡

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) የፖለቲካ ፕሮግራም ሰነድ | AFPO’s Manifesto

17

3.3.3 ባህል
የዳበሩና ጉልህ ባህሎች ይዘታቸው ሳይሸረሸር ለቀጣይ ትውልድ እንዲተላለፉ ይደረጋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በህዝባችን
ውስጥ ያሉ እና ያልጎሉ/ያልዳበሩ ባህሎች የሚያድጉበትና ለቀጣይ ትውልድ የሚሻገሩበት አሰራር ይዘረጋል፡፡ ጠንካራ
ባህላዊ እሴት ያለው ሕዝብ ለዛሬና ነገ ማንነቱ ያለው ድርሻ የጎላ መሆኑን በማመን ለባህላዊ እሴቶች፣ ወጎችና ልማዶች ልዩ
ጥበቃ ይሰጣል፡፡ ቱባ ባህሎች በመጤ ባህል እንዳይበረዙና ለትውልዱ ማንነታቸውን ሳይለቁ እንዲሻገሩ መንግሥት ያላሰለሰ
ጥረት ይደረጋል፡፡
3.3.4 ሚዲያ
ሚዲያ ለአንድ ሀገር እድገት መሰረት ከመሆኑም በላይ ዜጎች መረጃ የሚለዋወጡበትና ድምፃቸውን የሚያሰሙበት ትልቅ
ተቋም ነው፡፡ በሚዲያ ምክንያት አለም አንድ መንደር በሆነችበት በ21ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ሚዲያ የተቋማትና የዜጎች
የዕለት ከዕለት የህይወት አጋር ሆኖ ይገኛል፡፡
ስለሆነም ድርጅታችን የፕሬስ፣ ኤሌክትሮኒክና ሳይበር ሚዲያው በሁሉም ዘርፍ ተደራሽ፣ ነፃና ገለልተኛ ሆኖ እንዲሰራ በልዩ
አዋጅ ይቋቋማል፡፡ ጥራቱን የጠበቀና ያልተቆራረጠ የሚዲያ

Recent Developments

This page discloses what measures have been taken and what attempts are taking place currently to stop Amhara genocide, ethnic cleansing, and displacement by local and international actors. This page also exposes the usual deceptive tactics that Abiy Ahmed has mastered over the years to convenience current and future aid donors and financiers, such as the IMF and the World Bank, whenever Abiy is in dire need of foreign currency for doing business. No matter how difficult it is to document and publicize Abiy Ahmed’s daily criminal activities in remote and urban places in Ethiopia, AAN strives to document all available information from trustworthy news medias, such as the Internet, television and print

Members Commentary

AAN members share their opinions, comment on recent developments, suggest strategies on how to tackle and mitigate all sorts of problems targeting Amharas, etc.

Announcements

We announce future developments such as holding protests, fundraising, occasional meetings, and notifications coming from other Amhara organizations and the International Amhara Congress (IAC).

Research Article Articles pertaining to Amhara history, culture, religious affinity, demography, census, etc. are posted.

Video Gallery

Only selected videos and photos will be posted for public consumption

TOP